ቻይና የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ከ6 ወራት በኋላ ለዓለም ማሰራጨት እንደምትጀምር አስታወቀች።
የቤጂንግ ባዮሎጂካል ምርምር ኢንስቲትዩትና የቻይና ብሔራዊ ባዮቲክ ቡድን በጋራ እያዘጋጁት የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት 2 የምርመራ ፈተናዎችን አጠናቆ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ወይም በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ለገበያ ዝግጁ ሊሆን እንደሚችል ብሉምበርግ ዘግቧል። ቻይና የኮሮና ቫይረስ ክትባት በዚህ አመት በስፋት ለማምረት ዝግጅት እያከናወነች ሲሆን በየአመቱ ከ 100 ሚሊዮን እስከ 120 ሚሊዮን ክትባቶችን የማምረት አቅም ይኖራታል ተብሏል። […]