የኮሮና ቫይረስን ክትባትን ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት 40 አገራት ከ8 ቢሊዮን በላይ ዶላር ድጋፍ አደረጉ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ በሚል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ከመሪዎች ጋር ኦንላይን ባደረገው ስብሰባ 40 ሀገራት እና በጎ ፍቃደኛ ድጋፍ ሰጪዎች የየድርሻቸውን ለማወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

እስካሁንም 8 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በመሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ዘርፍ ውስጥ ባሉ ግለሰቦች ቃል የተገባ ሲሆን ድጋፍ የሚደረገው ገንዘብ ከክትባት ባለፈ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ለማከም የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሏል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አርሰላ ቮንዴር ሌየን እንዳሉት በገንዘብ ድጋፍ ላይ ከየሀገራቱ የሚታየው ተነሳሽነት ዓለምአቀፋዊነትን ከማጠናከር ባለፈ በአንድ የመተባበር ጥቅምን የሚያሳይ ቢሆንም ወደፊት ቫይረሱን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ብዙ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

እስካሁን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባትን ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽንና ኖርዌይ 1 ቢሊየን ዶላር፣ፈረንሳይ፣ጀርመንና ሳውድ አረቢያ 500 ሚሊየን ፓውንድ ፣ጃፓን 800ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቸውንም ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ ፣ሩሲያ እና ቻይና ስለ ድጋፉ ያሉት ነገር አለመኖሩን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

የአውሮፓ ህረብት ኮሚሽን ፕሬዝዳንቷ እንዳሉት በድጋፍ መልክ ከሚሰበሰበው ገንዘብ ላይ 4 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ክትባቱን ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት የሚውል ሲሆን 2 ቢሊየን ዶላር ለህክምና አንዲሁም 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ደግሞ ለተለያዩ ምርመራዎች እገዛ እንዲውል ተወስኗል፡፡

በአንድነት ተባብረን ለዓለም የሚተርፍ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ካገኘን የ 21 ኛው ክፍለ ዘመን ልዩ ዓለም አቀፋዊ የህዝብ በጎ ተግባር ሆኖ ይመዘገብልና ማታውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማግኘት በርካታ ጥናቶች በመከናወን ላይ ሲሆኑ የፋይናስ ድጋፍ እንኳን ቢደረግ የትኛው ክትባት ውጤታማ ነው የሚለውን ለማወቅ ረጅም ጊዜ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

አንዳንድ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ክትባቱን የማግኘቱ እና ለሁሉም እንዲደረስ የማድረጉ ሂደት እስከ አውሮፓውያኑ 2021 ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን ቫይረሱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶም ከ12 እስከ 18 ወራት ሊፈጅ ይችላል የሚሉ መላምቶች መቀመጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችች የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *