አልጄሪያ የኮሮና ቫይረስን በ15 ደቂቃ መመርመር የሚያስችል መሳሪያ ማምረት ጀመረች፡፡

አፍሪካዊቷ አገር አልጄሪያ በ15 ደቂቃ ውስጥ መርምሮ ውጤቱን ማሳወቅ የሚችል የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ (ኪትስ) ፈጣን በሚባል ደረጃ እያመረተች መሆኑን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡

በሳምንት 200 ሺ የመመርመሪያ መሳሪያ ኪትሶች እየተመረቱ ነውም ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ ዋና ከተማ አልጀርስ የሚገኘው ላብራቶሪ ካናዳ እና ጆርዳን ከሚገኙ በዚሁ ዘርፍ ከተሰማሩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን መሳሪያውን ማምረት መጀመሩም ነው የተነገረው፡፡

ሀገሪቱ ቫይረሱን ለመከላከል የህክምና መሳሪያዎችን እና የመድኃኒት ምርቶችን ከውጪ ለማስገባት 100 ሚሊዮን ዶላር መድባለች፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስም የንግድ እንቅስቃሴዎቿን እና የትራስፖርት አገልግሎቶቿን ለጊዜው አቁማለች፡፡

በአልጄሪያ አስካሁን 5ሺ 891 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 507 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡

2ሺ 841 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *