ሁለት ቻይናዊያን 250 ሺህ ዶላር ለናይጄሪያ ባለስልጣናት ጉቦ ሲሰጡ እጅ ከፍንጅ ተያዙ።

የናይጄሪያ የፀረ-ሙስና ኤጀንሲ እና የኤኮኖሚና ፋይናንስ ወንጀሎች ኮሚሽን (አይኤሲኤ) ሁለት የቻይና ዜጎችን በናይጄሪያ በሚኖሩበት አከባቢ ለሚገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት 250 ሺህ ዶላር ጉቦ በመስጠታቸው በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

ሜንግ ዌይ ኩን እና ዙ ኮይ ጉቦውን በሳጥን አድርገው ለባለስልጣናቱ ሲሰጡ ነው ማክሰኞ እለት የተያዙት ብሏል ኮሚሽኑ።

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በሚሠሩበት ናይጄሪያ ውስጥ በሚገኘው የቻይና የግንባታ ኩባንያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን በተመለከተ ለሚመሰረተው ክስ ምርመራ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ለመንገዶች እና ለውሃ ፕሮጄክቶች ኮንትራቶች ክፍያ የተፈጸመውን 130 ሚሊዮን ዶላር ሙስናን እየመረመረ መሆኑን ገልጻል፡፡

እንዲሁም ሌሎች የገንዘብ ማጭበርበሮችን ክሶች እየመረመረ ነው ፡፡

ኮንትራቶቹ በ 2012 እና በ 2019 ዛምፋራ ግዛት ለሚገነቡ ስራዎች ከናይጀሪያ ለቻይናው ዞንጓ የተሰጡ ነበሩ።

የቻይናው ኩባንያም ሆነ ኃላፊዎቹ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዳልሰጡ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከሙስና ጋር የተዛመዱ የውጭ ኩባንያዎች ባለሥልጣናት ናይጄሪያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሲውል እምብዛም አይስተዋልም ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.