ከናይጄሪያ ከተሞች አንዷ በሆነችው ሌጎስ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የነበሩ እና የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው የቆዩ የ98 ዓመት አዛውንት ከቫይረሱ ማገገማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የከተማዋ ገዢ ከአዛውንቷ በተጨማሪ ሌሎች 25 ሰዎችም ከቫይረሱ ማገገማቸውን አስታውቋል፡፡
አዛውንቷ በከተማዋ ከቫይረሱ ካገገሙ ሰዎች በእድሜ ትልቋ ሆነው ተመዝግዋልም ተብሏል፡፡
ሌጎስ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተባቸው የናይጄሪያ ከተሞች ትልቁ ቁጥር የሚገኝባት ነች፡፡
በናይጄሪያ ከተመዘገበው 4ሺ 971 የከሮና ቫይረስ ኬዝ 2ሺ 41ዱ በሌጎስ የተመዘገበ ሲሆን 33 ሞት በዚህችው ከተማ ተመዝግቧል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በትግስት ዘላለም
ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም











