በአዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ ከቀጣዩ ሰኞ ጀምሮ የቪዛ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአዲስ አበባ የሚገኙ ኢምባሲዎች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው ይታወሳል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኢምባሲ ግን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የቪዛ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

ኤምባሲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ከሆነ በቦሌ ከሚገኘው ስናፕ ፕላዛ የአገልግሎት ማእከሉ ከግንቦት 10 ጀምሮ የቪዛ አገልግሎት መስጠት ይጀመራል።

የኢትዮጵያ እና የቱርክ ዲፕሎማሲዊ ግኑኝነት1933 አመተ ምህረት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በመልካም ሁኔታ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስር ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን ከ500 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች በጨርቃጨርቅ፣ኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

ቱርክ በተለይ በኢትዮጵያ በአዋሽ ኮምቦልቻ የባቡር መስመር ዝርጋታ በመስራት አጋርቷን እያሳየች ትገኛለች፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ቱርክ ቡና፣አበባ፣የቅባት እህሎች እና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ወደ ቱርክ በመላክ ላይ ትገኛለች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *