በአዲስ አበባ ጀርመን አደባባይ በተፈጠረ ከባድ የእሳት አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው በትናንትናው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 2 የእንጨት እና ችቡድ ማምረቻ ድርጅት ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

በዚህ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 5 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት አጋጥሟቸዋል ብሏል።

አደጋውን ለመቆጣጠር ከ100 በላይ የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን የወደመው ንብረት ከባድ በመሆኑ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

ትናንት 10 ሰዓት ላይ እንደተከሰተ የተገለጸው ይህ አደጋ ሌሊት 8 ሰዓት ላይ መቆጣጠር እንደተቻለም ተገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.