ሀገራቸውን እየመሩ ያሉና ቀደም ሲል ሀገራቸውን በጠቅላይ ሚስትርነትና በፕሬዝዳንተነት ያገለገሉ ፣ ከ140 በላይ መሪዎች ፣ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከክፍያ ነጻ እንዲሆን መጠየቃቸው ተነግሯል ።
ክትባቱ የፈጠራ የባለቤትነት መብት እንዳይጠየቅበት እና ህክምናውም ነጻ እንዲሆን መሪዎቹ ጠይቀዋል ተብሏል ።
አልጄዚራ እንደዘገበው ፣ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከክፍያ ነጻ እንዲሆን ከጠየቁ የሀገር መሪዎች መካከል የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪያል ራማፎዛ እና የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሀን እንደሚገኙበት ተገልጿል ።
ቀደም ሲል ሀገራቸውን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እና በፕሬዚደንትነት ያገለገሉት እንደ ጆሴ ማኑኤል ባሮሶ፣ ጎርደን ብራውን እና ኤለን ጆሴፍ ሰርሊፍ ክትባቱ ከክፍያ ነጻ እንዲሆን ከጠየቁት የቀድሞ ሀገር መሪዎች መካከል ናቸው ተብሏል ።
የአለም ጤና ድርጅት አካል የሆነው የአለም ጤና ጉባኤ ( WHA ) በሚቀጥለው ሳንምት አመታዊ ጉባኤ ያካሄድል ፣ የሀገሪቱ መሪዎች ጥያቄም በዚሁ በጉባኤ ይቀርባል መልስም ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
የመሪዎችን ፊርማ የያዘው እና ለ WHA የቀረበው ደብዳቤ ተቀባይነት እንዲያገኝ የሁሉም አለም ሀገራት መንግስታት እና አለም አቀፍ ተቋማት በጋር መቆም አለባቸው ብለዋል መሪዎቹ ።
ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የሆነ ክትባት ሲገኝ በሁሉም የአለም ሀገራት በፍጥነት እንዲሰርጭም ጠይቀዋል።
በተመሳሳይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከልከል እና ለመቆጣጠር የሚያገለግል ማንኛውም ቴክኖሎጂ ከክፋያ ነጻ እንዲሆን ተጠይቋል ።
የአሜሪካን መንግስት ክትባቱን ለማግኘት በሚደረገው የምርምር ሂደት የገንዘብ ድጋፍ እያደረገች በመሆኑ ክትባቱን ቅድሚያ እንድታገኝ ይደረጋል ተብሏል ።
የፈረንሳይ መንግስት በበኩል ክተባቱ ለአሜሪካ ቅድሚያ ይሰጣል መባሉ ተገቢ አይደለም በማለት ማጣጣሉ ተነግሯል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በዳንኤል መላኩ
ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም











