የሶማሊያ ጦር በደቡባዊ የሃገሪቷ ክፍል ሰድስት የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ፡፡

በሃገሪቷ ደቡባዊ ክፍል ረቡእ እለት በተካሄደ ዘመቻ ስድስት የአሸባሪ ቡድኑን ታጣቂዎች መግደሉን የሃገሪቷ የጦር መኮንን ትናንት አስታውቀዋል፡፡

የሶማሊያ እግረኛ ጦር ኮማንደር አብዲ ሃሚድ ሞሃመድ ድሪር እንደተናገሩት በጃኔልና ቁርዬሌ ከተሞች መካከል ባሉ መንደሮች በተካሄደ አሰሳ ነው ታጣቂዎቹ የተገደሉት፡፡
ቀደም ብሎ መረጃው እንደነበራቸውም ነው የተናገሩት፡፡

ከተገደሉት ውስጥም ነባር የአልሻባብ ተዋጊ የሆነው አብዲ ሙሲን ሁሴን እንደሚገኝበትም ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡

አሁን ጦራችን አካባውን ተቆጣጥሮታል ታጣቂዎቹም ወደ ጫካ ተመልሰዋል ነው ያሉት፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ በቡላ ሼክ መንደር በመንግስት ጦርና በታጣቂዎች መካከል በተከፈተ የኩስ ልውውጥ የአልሻባብ ወታደሮች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

ሂንዲ ኤደን የተባለ የአካባቢው ነዋሪ በሁለቱም ወገኖች መካከል የተኩስ ልውውጥ ነበር፡፡

በስተመጨረሻ ግን የቶር ሃይሉ አሸንፎ አካባቢውን ተቆጣጥሮታል ሲል ለሲጂቲኤን አፍሪካ ተናግሯል፡፡

የሶማሊያ ጦር ሃይል በከተሞች አካባቢ የሽብር ቡድኑ ላይ እርምጃ ቢወስድም በገጠሩ አካባቢ ግን አሁንም ይንቀሳቀሳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባይነሽ ሽባባው
ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.