በሮም የኢትዮጰያ ኤምባሲ መደበኛ ስራውን ጀመረ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረው በሮም የኢትዮጵያ ኢምባሲ መደበኛ ስራው ከዛሬ ጀምሮ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንየት ስራው ተገድቦ የቆየው ኢምባሲው ስራው ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ ስራው አንደሚመለስ አስታውቋል፡፡

ኤምባሲው ለበሽታው ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ መደበኛ ስራው አንደሚያከናውን ተናግሯል፡፡

ከኢትዮ ጣሊያን ጦርነት በኃለ ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነታቸውን በማሻሻል ጣሊያን በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን የከፈተች ሲሆን ኢትዮጵያም በሮም ኤምባሲዋን ከፍታለች፡፡

ታሪካዊ ወዳጅነት ያላቸው ኢትዮጵያ እና ጣልያን በሁለትዮሽ፣ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በትብብር በመስራት ላይ ናቸው።

ጣልያን ከአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት መካከል ሶስተኛዋ አገር ናት።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.