የፊሊፒንሱ ፕሬዘዳንት አገራቸው የጀመረችውን የጸረ አደንዛዥ ዘመቻን አጣጥሏል ያሉት የቴሌቪዥን ጣቢያን አገዱ።

የፊሊፒንስ ፕሬዘዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ ABS-CBN የተባለውን የሀገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭቱ በአገራቸው እንዲቋረጥ ማዘዛቸው ተሰምቷል።

ፕሬዘዳንት በጣቢያው ላይ እርምጃ የወሰዱበት ምክንያት ደግሞ ሀገሪቱ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመግታት የምታካሂደውን ጥረት አናንቋል ወሳኝ የጋዜጠኝነት ተግባሩንም አልተወጣም በሚል ማገዳቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ዱተርቴ ይሄንን ስርጭት ውጭ ለማድረግ ለረጅም ጊዜ ሲያስፈራሩ መቆየታቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ከዚህ ባሻገር ኮቪድ-19 በመጠቀም በሆንግ ኮንግ ያለውን ተቃውሞ ለመግታት እንደ ሽፋን ሆኖ እያገለገለ ነው በሚል ከስርጭት መውጣቱ ተገልጿል፡፡

ነገር ግን የፍሊፒንስ መንግስት እንዳለው ቴሌቪዝን ጣቢያው የኔትዎርክ ስርጭት ጊዜው እንዳለፈበት ገልፆ እርሱን ሲያስተካክል ስርጭት ማካሂድ እንደሚችል ገልጿል፡፡

አሁን ላይ ፕሬዘዳንቱ ሲመኙት የነበረውን የቴሌቪዥን ጣቢያ ከስርጭት ውጭ ማድረጋቸው በመሳካቱ በሀገሪቱ ያሉ ሌሎች የሚዲያ ጣቢያዎች ላይ መቼ ሊዘመትባቸው እንደሚችል እርግጠኛ ባለመሆናቸው ስጋት ገብቷቸዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዘዳንት ዱተርቴ አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎች በቀጥታ በፖሊስ እንዲገደሉ ትዕዛዝ በማስተላለፋቸው እና ፖሊሶችም እርምጃውን ተግባራዊ በማድረጋቸው የሰብአዊ መብት ተቋማት ትችቶችን ይሰነዝሩባቸዋል።

ይሁንና በአደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎች የተማረሩት የፊሊፒንስ ዜጎች ግን ለፕሬዘዳንቱ የተለየ ፍቅር እንዳላቸው ይናገራሉ።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *