የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር መልቀቂያ አስገቡ፡፡

በቀድሞ ሚስታቸው የግድያ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት መመላለስ ከጀመሩ የሰነባበቱት እና በዚህም ከፍተኛ ጫና ውስጥ የወደቁት የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር ቶማስ ታቤን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መቼ ቢሮአቸውን ለቀው እንደሚወጡ የታወቀ ነገር ባይኖርም ፓርቲያቸው ግን በነገው እለት የተመረጠው አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሐላ እንሚፈፅም አስታውቋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣኔ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ላሳውቃችሁ እወዳለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በቃል መናገራቸውን ኤ ኤፍ ፒ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

በትግስት ዘላለም
ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *