የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር እና የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ባለቤታቸው አንጀሊና ቴኒ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡

በርካታ የሪክ ማቻር የስራ ባልደረቦች እንዲሁም የግል ጠባቂዎችም በቫይረሱ መያዛቸው ተነግሯል፡፡

ማቻር ራሳቸውን ለ14 ቀናት በቤታቸው አግለው እንደሚቆዩም በሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ በኩል አስታውቀዋል ሲል ሮይተረስ ዘግቧል፡፡

በደቡብ ሱዳን አስካሁን 347 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 6 ሰዎችም በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *