ጀርመንና ፈረንሳይ አውሮፓን ሙሉ በሙሉ በመዝጋታቸው መቆጨታቸውን አሳወቁ ።

የአውሮፓ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን ለመታደግ ህብረቱ 500 ቢሊዮን ዩሮ እንዲለቅ በፈረንሳይና በጀርመን ታቅዷል
የፈረንሳይና የጀርመን መሪዎች አውሮፓ በኮሮና ምክንያት ከጋጠማት የኢኮኖሚ ድቀት እንድታገግም 500 ቢሊዮን ዩሮ ፈንድ እንዲደረግ አቅደዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ቀድሞውንም በነበረው የብድር ስርአት ለህብረቱ አባል ሀገራት በብድር መልክ ከቀረበው 540 በሊዮን ዩሮ በተጨማሪ ነው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማንዬል ማክሮንና የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርክል 500 ቢሊዮን ዩሮ ፈንድ የማድረግ ዕቅድ ያወጡት፡፡

ይሄ ገንዘብ እንዲለቀቅ በ ሀያ ሰባቱ የህበረቱ አባል ሀገራት መፅደቅ አለበት።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ይሄን ያሳወቁት በጋራ በቪዲዮ ኮንፍረንስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን እርዳታው በብድር ሳይሆን በስጦታ ነው መሰጠት ያለበት ሲሉ የጀርመኗ ቻንስለር ኤንጌላ መርክል ደግሞ ወጪው ከወደፊት የአውሮፓ ህብረት በጀት ላይ የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል፡፡

ከ 2008 በኋላ በአውሮፓ የከፋው የኢኮኖሚ ቀውስ ነው በኮሮና ምክንያት የተከሰተው።

ፈንዱ በፈረንሳይ፣ጣልያን እና ለየላ የተወሰኑ ሀገራ ገፋፊነት እዳን በጋራ ለመካፈል በጀርመን የተወሰደ እምጃ ነው የተባለ ሲሆን ይሄ ጉዳይ የህብረቱ መፋጫ ጉዳይ ሆኖ የከረመ ነው፡፡

ሁለቱም መሪዎች በወረርሽኙ ምክንያት የረዥም ጊዜ ጉዳት ያለውን ድንበር መዝጋትን ጨምሮ አውሮፓን ሙሉ በሙሉ መዝጋታቸው እንደቆጫቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *