በአማራና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ 41 የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ 9 ሺህ ቀስቶች ተያዙ።

በአማራና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ 41 የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ 9 ሺህ ቀስቶች ተያዙ።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ም/ል ኮሚሽነር ነጋ ጃራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በሁለቱ ክልል ዞኖች በተቋቋሙት ኮማንድ ፖስቶች አማካኝነት 41 የጦር መሳሪያና 9 ሺህ ቀስቶች መቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል፡፡

በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ዞኖች ላይ ወንጀሎችን እያባባሱ የሚገኙት ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ናቸው ያሉት ም/ል ኮሚሽነር ነጋ እነዚህ የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ በአዊና መተከል ዞን ላይ የተደራጀው ኮማንድ ፖስት አበረታች ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ዞኖች ላይ ቀስትን ጨምሮ ማናቸውንም የጦር መሳሪያ ከቦታ ቦታ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን በክልሎቹ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መግለፁ ይታወቃል፡፡

በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ዞኖች ላይ በየጊዜው የሚነሳው የፀጥታ ችግር ዳግም እንዳያገረሽ የተደራጁ ኮማንድ ፖስቶች አስፈላጊውን የህዝብ ግንኙነት ስራ አጠናክረው እየሰሩ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የአማራና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ህዝብ ከዚህ ቀደም ለዘመናት ተዋልዶና ተሳስሮ በፍቅር ፤ በአንድነት ይኖር የነበረ ማህበረሰብ ነው ያሉት ሀላፊው ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡

በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ከዚህ በፊት በተከሰተ ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ከ13 ሺህ በላይ ዜጎች ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ቀድሞ መኖሪያ ቀያቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ግንብት 13 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *