ደቡብ ኮሪያ በኮሪያ ጦርነት ለተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦች 40 ሺህ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ለገሰች።

አገሪቱ ለኢትዮጵያዊያኑ ድጋፍ ያደረገችው በአዲስ አበባ በሚገኘው የደቡብ ኮሪያ ኢምባሲዋ በኩል መሆኑን ኢምባሲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ኢምባሲው እንዳለው የአፍ እና የፊት መሸፈኛው እራሳቸውን ከአስከፊው የኮሮና ወረርሽሽኝ እራሳቸውን እንዲጠብቁ ያስችላል።

ይህ 40 ሺህ የፊት እና የአፍ መሸፈኛ ለ132 ኢትዮጵያዊያን የተሰጠ ሲሆን ድጋፉ የኮረሪያ ጦርነት 70ኛ ዓመትን የማክበር አንዱ አካል ነውም ተብሏል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ኮሪያ በአስከፊ ጊዜ በነበረችበት ወቅት ኢትዮጵያዊያኑ የከፈሉት መስዋዕትነት ዘላለማዊ ነው፣ ይህ መስዋዕትነት ደግሞ የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ዘላማዊ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ይፋዊ የዲፕሎማሲ ወዳጅነታቸውን ከጀመሩ ከ70 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር በ1950 በተካሄደው የኮሪያ ጦርነት ኢትዮጵያ ከሌሎች 20 የዓለማችን አገራት መካከል ወደ ኮሪያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ከላኩ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን ከአፍሪካ ደግሞ ብቸኛዋ ነበረች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ግንቦት 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.