የሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አራት አዲስ ሹመቶችን በማጽደቅ አጠናቀቀ።

በትናንትናዉ ዕለት የ12 የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት ያነሳው
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ረፋድ አጠናቋል።

ምክርቤቱ በዛሬው እለት አዳዲስ ሹመቶችን ያፀደቀ ሲሆን
1.ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ ቃሲም/ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ

2.አቶ አሊ በደን አደን ማህመድ/ ኮምዪኔኬሽን ቢሮ ሃላፊ

3.አቶ አብዲቃድር ረሽድ /የፐብሊክ ሰርቪስ ኃላፊ

4. አቶ አብዲ ማህመድ / የማእድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

በመሆን ቃለ መሀላ መፈፀማቸውን የሶማሌ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ም/ቤቱ በትናንትናው እለት ባካሄደው ጉባኤ በሙስና፣በማህበረሰቡ መካከል ሁከት በመፍጠርና ሥርዐት አልበኝነት እንዲሁም በሌሎች ወንጀሎች ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን 12 የምክርቤት አባላትን ያለ መክሰስ መብት ማንሳቱ አይዘነጋም።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *