ዛሬ ምሽት ቡንደስሊጋ ሄርታ በርሊን ከ ኡኒየን በርሊን ያገናኛል።

ሁለቱ ክለቦች የምስራቅ እና ምዕራብ በርሊን ተወካዮች ናቸው ። በሁለቱ ቡድኖች መካከል ባለፈው ህዳር የተደረገው ጨዋታ የማይረሳ ነው። ደጋፊዎች ተቀጣጣይ ነገሮችን ወደ ሜዳ በመወርወራቸው ጨዋታው ለደቂቃዎች ተቋርጦ ነበር። ኡኒየን በርሊን የማሸነፊያዋን ጎል ያስቆጠረው መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቅቆ በተጨመረው የባከነ ሰዓት 10ኛው ደቂቃ ላይ ነው። ዛሬ በኦልምፒክ ስታዲየም ከሄርታ በርሊን ጋር የሚደረገው ጨዋታ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በዝግ ስታዲየም ይከናወናል ። “የህዳሩ ጨዋታ የማይረሳ ነበር ። ብዙዎች ያስታውሱታል ። ጥቁር ቀን ነበር።

አሁን ያነ ቀን ከኋላችን ትተን ወደ ፊት የምንሻገርበት ዕድል አግኝተናል” ብለዋል የሄርታ በርሊኑ ጀነራል ማናጀር ማይክል ፕሪትዝ ። ” አሁን ላይ ብዙ ነገሮች ተለዋውጠዋል። የደርቢው ጨዋታም የተለየ ስሜት ይኖረዋል” በማለት የሄርታ በርሊኑ አሰልጣኝ ብሩኖ ላባዲያ ያክላሉ። አሰልጣኙ የሄርታ በርሊን አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት በቅርቡ ነው። ባሳለፍነው ቅዳሜ በሄርታ አሰልጣኝነት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ሆፈንሄይምን በማሸነፍ ጀምረዋል። የኡኒየን በርሊኒ አሰልጣኝ ኡርስ ፊሸር ቡድናቸው ባለፈው ሳምንት በባየር ሙኒክ 2ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ እንዳልነበሩ ይታወቃል።

ያልተገኙት ቤተሰባዊ በሆነ ጉዳይ ነበር። በዛሬው ጨዋታ ግን ይመለሳሉ ። ” ምንም እንኳን ሁኔታዎች ከወትሮው የተለዩ ቢሆንም ለዛሬው ጨዋታ ተዘጋጅቻለሁ ” ብለዋል። ” ዞሮ ዞሮ የደርቢ ጨዋታ ነው። ብዙ ስሜት የሚንጸባረቅበት የተለየ ተጫዋች ነው። ተጫዋቾችን ከማነሳሳት ብዙ መድጀም አይጠበቅብኝም። እኔ በግሌ የማስቀድመው ግባችንን ማሳካት ነው። በሊጉ መቆየት እፈልጋለሁ ።

 ሄርታን ማሸነፍ ግባችንን እንድናሳካ ያግዘናል ” ብለዋል። ኡኒየን በርሊን በቡንደስሊጋው ተሳታፊ መሆን የቻለ የመጀመሪያው የምስራቅ በርሊን የመጀመሪያው ክለብ ነው ። አሁን ላይ ከወራጅ ቀጠናው በሰባት ነጥብ በሰባት ነጥብ ርቆ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሄርታ በአንድ ነጥብ እና በአንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ተቀምጧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.