ዩናይትድ በኮቪድ 19 ምክንያት 28 ሚ.ፓ አጣ::

የውድድር ዘመኑ በኮሮና ቫይረስ በተቋረጠበት ወቅት ዩናይትድ አምተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር። ማንቸስተር ዩናይትድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እስካሁን 28 ሚ.ፓ እንዳሳጣው እና መጠኑ ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግሯል። ዩናይትድ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የፋይናንስ ሪፖርት ትላንት ይፋ አድርጓል። የፋይናንስ ክፍሉ ሃላፊ ክሊፍ ባቲ ፕሪምየር ሊጉ ወደ ውድድር ተመልሶ ቢጠናቀቅ እንኳን 20 ሚ.ፓ የቴሌቪዥን ስርጭት መብት ገዝተው ለነበሩ ተቋማር መመለሱ እንደማይቀር ተናግረዋል። ።

ማንቸስተር ዩናይትድ በመጋቢት ወር ያደርጋቸው የነበሩ ሶስት ጨዋታዎች በመተላለፋቸው ተጨማሪ 8 ሚ.ፓ አጥቷል። በወረርሽኙ ምክንያት በድምሩ 11 የማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታዎች ተላልፈዋል። የፋይናንስ ሪፖርቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ በተደረገ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ባቲ ዩናይትድ 20 ሚ.ፓ ለቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያዎች የሚመልስበትን ምክንያት አስረድተዋል። ዋነኛው ምክንያት ጨዋታዎቹ የሚከናወኑት አስቀድሞ ከተያዘላቸው ቀን እና ሰዓት ውጪ በመሆኑ እንደሆነ ገልጸዋል። ዩናይትድ በወረርሽኙ ምክንያት ይደርስብኛል ብሎ የሚያስበውን አጠቃላይ ኪሳራ እንዲያሳይ ተጠይቆ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።

የክለቡ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤድ ዉድዋርድ ግን ከፍተኛው ጫና የሚያርፈው እስከ ሰኔ 30 በሚዘልቀው ሩብ ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። በሩብ ዓመቱ ገቢው በ18.7 ቀንሷል። የክለቡ ዕዳ ከ124.4 ሚ.ፓ ወደ 429.1 ከፍ ብሏል። ባቲ አያይዘውም መጋቢት 15 ወደ ለንደን አምርተው ቶተንሃምን ይገጥሙበት የነበረው ጨዋታ በመተላለፉ ብቻ ክለባቸውን 4 ሚ.ፓ አሳጥቶታል። በማንቸስተር ዩናይትድ የ142 ዓመት ታሪክ እጅግ አስከፊው ጊዜ ምናልባትም ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ሊሆን እንደሚችል ውድዋርድ ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም


FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *