ግብፅ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር አቋርጣው የነበረውን የሶስትዮሽ የህዳሴ ግድብ ውይይት ለመቀጠል ተስማማች።

ኢትዮጵያ በመጭው ክረምት የህዳሴው ግድብ ውሀ መያዝ ይጀምራል ማለቷን ተከትሎ ግብጽ የኢትዮጵያን እቅድ ለማሰናከል የተለያዩ ተንኮሎችን ስታቀነባብር ቆይታለች።

ከተንኮሎቹ መካከልም ኢትዮጽያ የአባይ የታችኛው ተፋሰስ አገራትን በውሀ ድርቅ ልታስመታ የናይል ወንዝን ልትዘጋ ነው በሚል ለአረብ አገራት እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሳሳተ መረጃ ስትሰጥ ቆይታለች።

ላለፉት 8 ዓመታት ከኢትዮጵያ ጎን የነበረችው ሱዳንን በግድቡ ላይ ያላትን አቋም ለማስቀየር የተለያዩ ሴራዎችንም ከአሜሪካ እና ሌሎች አገራት ጋር በመሆን ጫና ስታደርግም ቆይታለች።

እንዲሁም ኢትዮጵያ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር ሳትወያይ በቀጣይ ክረምት የህዳሴው ግድብ ውሀ መያዝ ልጀምር በማለቷ የተባበሩት መንግስታት የጽጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን ከዚህ ድርጊቷ ያስቁምልኝ ስትልም ከሳት ነበር።

ኢትዮጵያም በኒዮርክ በሚገኘው አምባሳደሯ እና በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በኩል በወንዜ ላይ ከእኔ ውጭ ማንም የመወሰን ስልጣን የለውም ስትል ምላሽ መስጠቷ ይታወሳል።

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝም ግብጽ በዚህ ጉዳይ ላይ ከአራት ዓመት በፊት ማለትም እንደ ጎርጎሮሲያውያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 በካርቱም በፈረሙት ስምምነት መሰረት ዳግም ወደ ውይይት ብትመለስ ሲል ምክረሀሳቡን ሰንዝሯል።

በመጨረሻም አማራጭ ያጣችው ግብጽ ከኢትዮጵያ እና ሱዳን ጋር ለመወያየት ወደ ዳግም ውይይት ለመመለስ መወሰኗን በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ በኩል ማሳወቋን ዴይሊ ኒውስ ኢጅፕት የተሰኘው የግብጽ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *