በሐኪሞቿ ላይ በሚደርስ ጥቃት የተማረረችው ሱዳን የህክምና ባለሙያዎችን ደህንነት የሚጠብቅ የፖሊስ ሀይል ልታቋቁም ነው፡፡

የሱዳን የመንግስት ባለስልጣናት ለአልጀዚራ እንደተናገሩት የህክምና ባለሙያዎች የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል የፖሊስ ሀይል ሊቋቋም እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘም በሱዳን በሆስፒታሎች እና በጤና ባለሙያዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈጸመ ይገኛል ተብሏል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ በህክምና ባለሙያዎች ላይ ያነጣጠረ ሁለት ጥቃቶች የተፈጸሙ ሲሆን በርካታ የህክምና ባለሙያዎችም ጉዳት ማስተናገዳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብድላ ሀምዶክ ከሐኪሞች ተወካይ ጋር ተገናኝተው በተደጋጋሚ በህክምና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በተገቢው መንገድ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ እንደመከሩና ከስምምነትም እንደደረሱ ተናግረዋል።

በዚህም የህክምና ባለሙያዎቹን ደህንነት የሚያስጠብቅ የፖሊስ ሀይል ሀገራቸው ልታቋቁም እደወሰነች ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአልጄዚራ የተናገሩት፡፡

በሱዳን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት እርብርብ እያደረጉ ባሉት የህክምና ባለሙያዎች ላይ ጥቃት እየተደጋገመ በመምጣቱ ምክንያት በመዲናዋ ካርቱም በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና ስርአቱ መቋረጡ ዘገባው ጠቁሟል።

በሱዳን በኮሮና ተያዙ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 380 የደረሰ ሲሆን 63 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *