ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዎች ላይ የሚደረገው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዛሬ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ ተጀምሯል፡፡

NVX-CoV2373 የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ክትባት የተመረተው በአሜሪካ ኩባንያ ኖቫቫክስ ነው ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሙከራ የሚደረግባቸው 130 ጤናማ ጎልማሶች ላይ ሲሆን ውጤቱ ሀምሌ ላይ እንደሚታወቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በመላው ዓለም የሚገኙ ተመራማሪዎች ከ100 በላይ ኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችሉ ክትባቶች ለማግኘት ጥረት ላይ ናቸው። ከወር በፊት በእንግሊዝ በሰዎች ላይ የሚደረገው የክትባት ሙከራ መጀመሩ አይዘነጋም፡፡

በአውሮፓ የመጀመሪያ የሆነውን ሙከራ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያስጀመሩት ሲሆን የክትባቱ ውጤታማነት የሚታወቀው ከወራት በኋላ ነው ተብሎ ነበር።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *