ላለፉት 35 ቀናት ዜጎቿን በኮሮና ምክንያት ስታጣ የቆየችው አየርላንድ ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ምንም የኮሮና ሞት ሳታስመዘግብ ቀኑን አሳልፋለች።

ዛሬ አየርላንድ ምንም የኮሮና ሞት ሳይሰማባት ቀኑን ያሳለፈች ሲሆን እንደ አውሮፓውያኑ ከመጋቢት 21 በኋላ ከኮሮና ጋር በተያያዘ ያልምንም ሞት ያሳለፈችው ቀን ሆኖ አልፏል።

እስካሁን በአየርላንድ 1 ሺህ 606 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በአየርላንድ፡፡

59 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና የተጠቁ ሲሆን አጠቃላይ በኮሮና የተያዘው ሰው ቁጥር 24 ሺህ 698 ደርሷል፡፡

ባለፈው ሳምንት የአየርላንድ ዋና የህክምና ሀላፊው ቶኑ ሆሎሀን ውጤታማ በሆነ መልኩ ኮሮና ከማህበረሰባችን እየተፋ ነው ብለው ነበር፡፡

እንደ አውሮፓውያ ከ ሰኔ 8 በኋላ የቤት ለቤት ጥየቃና የሸቀጥ ሱቆች ክፍት እንዲሆኑ ይፈቀዳል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት

ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.