በኢትዮጵያ ተጨማሪ 46 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ተጨማሪ የአንድ ሰው ሞት መመዝገቡን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,410 የላብራቶሪ ምርመራ አርባ ስድስት (46) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ አንድ (701) ደርሷል፡፡

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው – 34

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው – 4

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው – 8

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስምንት (8) ሰዎች (ሁለት ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል እና ስድስት ሰዎች ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ስልሳ ሰባት (167) ደርሷል።

እንዲሁም የ 32 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበረች ኢትዮጵያዊት ትናንት ሌሊት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስድስት (6) ደርሷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *