በጀርመን ቡንደስሊጋ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

በጀርመን ቡንደስሊጋ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ባየር ሊቨርኩዘን ከ ዎልስፍበርግ አይንትራክት ፍራንክፈርት ከ ፍሬይቡርግ ቨርደር ብሬመን ከ ቦሲያ ሞንቼግላድባክ እና በጉጉት የሚጠበቀው ደር ክላሲከር በቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ባየርን ሙኒክ መካከል ይከናወናል። ሃንሲ ፍሊክ የዛሬው የባየርን ሙኒክ እና ዶርትሙንድ ጨዋታ የዋንጫ አሸናፊውን አይወስንም ብለዋል።

በአሊያንዝ አሬና የሚደረገውን ጨዋታ የቡንደስሊጋው መሪ ባየርን ካሸነፈ የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ ስድስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከዶርትሙንድ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ያሰፋል። ፍሊክስ ግን “የዛሬው ጨዋታ ውጤት ምንም ይሁን ምን የሚወስነው ነገር የለም ” ብለዋል።

ዶርትሙንድ ባሳለፍነው ቅዳሜ ዎልፍስበርግን 2ለ0 ሲያሸንፍ በእረፍት በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ የወጣው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሀል ተከላካይ ማትስ ሀመልስ ለዚህ ጨዋታ ብቁ መሆን ቢችል ብሎ ተስፋ አድርጓል። ዶርትሙንድ በዚያ ጨዋታ ያስመዘገበው ድል ከባየርን ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ አጥብቦለት ነበር። ነገር ግን በማግስቱ እሁድ አይንትራክት ፍራንክፈርትን 5ለ2 ያሸነፈው ባየርን ልዩነቱን መልሶ የአራት ነጥብ አድርጎታል።

እንደ ዶርትሙንድ ሁሉ ባየርንም የውድድር ዘመኑ ዳግም ከተጀመረ በኋላ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች አሸንፏል። ባየርን የሚጫወተው ስምንተኛ ተከታታይ የቡንደስሊጋ ዋንጫውን ለማንሳት ነው። ባለፈው ህዳር ኒኮ ኮቫችን ተክተው ሃላፊነቱን ለተረከቡት ፍሊክስ ግን የመጀመሪያቸው ይሆናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *