ናይጀሪያ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ምግብ ከውጭ አገራት ማስገባት ልታቆም መሆኑን አስታወቀች።

የናይጄርያው ፕሬዝዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ የናይጄርያ ገበሬዎች ሙሉ ህዝቡን የሚመግብ በቂ ምግብ ማምረት አለባቸው ብለዋል።

ሀገሪቷ ከውጪ ምግብ ለማስገበት የሚሆን ምንም ገንዘብ የላትም ብለዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተከትሎ ፤በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት የሚፈጠር የምግብ ዋስትና ስጋት የገባቸው ሁሉ አስተያየት እየሠጡ ነው፡፡ በተለይ በመላው አፍሪካ እየተፈጠረ ያለው የምግብ መሸጫ ዋጋ ንረት አሳሳቢ እንደሆነ ከየአቅጣጫ የሚመጡ ሀሳባች እንደሚያመላክቱ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

እንደ ተባበሩት መንገስታት ድርጅት የምግብና ግብርና ፕሮግራም ከሆነ ከኮሮና ቀውስ በፊትም ገበሬዎች 200 ሚሊዮን የሚሆነውን የናይጄርያን ህዝብ የምግብ ፍላጎት ማርካት አልቻሉም፡፡ምንም እንኳ የግብርናው መስክ ሰራተኛውን በመቅጠር ቀዳሚው ቢሆንም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በአብዛኛው ከነዳጅ በሚገኝ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ችላ ተብሎ ኖሯል፡፡ናይጄርያ ለተወሰነ ጊዜ የሀገር ውስጥ የሩዝ ምርቷን ከፍ ለማድረግ እየሞከረች ነበር፡፡

በተለይም ባለፈው አመት ከታይላንድ በህገ ወጥ መንገድ የሚገቡ ምርቶች ላይ የየብስ ድንበሮችን እስከ መዝጋት ጠንካራ እርምጃዎችን ወስዳለች፡፡

ከእገዳው በፊት ናይጄርያ ሚሊዮን ቶኖች ሩዝ በየአመቱ ከታይላንድ ታስገባ ነበር፡፡

አሁን ከውጪ የሚገቡ ሩዙች በወደብ በኩል እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ የገቢ ግብር ተጥሎባቸዋል፡፡

የኮሮና ቀውስ ከተከሰተ አንስቶ በናይጄርያ የምግብ ዋጋ መጨመሩን እንደቀጠለ ሲሆን የመንግስት ገቢ ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በመውረዱ ምክንያት ክፉኛ ተጎድቷል፡፡

የአፍሪካ ትልቋ ኢኮኖሚ ናይጄርያ በሚቀጥለው አመት በ1 ነጥብ 5 በመቶ እንደምታሽቆለቁል የአለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ (አይ ኤም ኤፍ) ትንበያ ያስረዳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት

ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.