ዓለም ለሁለተኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እራሷን እንድታዘጋጅ የዓለም ጤና ድርጅት አሳሰበ።

አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምርመራን ካላሳደገች “ድምፅ አልባ” ወረርሽኝ ሊከሰትባት እንደሚችልም ድርጅቱ አስጠንቅቋል፡፡

አፍሪካውያን እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የከፋ ጉዳትን አላስተናገዱም ነገር ግን የሚደረገውን ምርመራ ካላሳደጉ በአህጉሪቱ ድምፅ አልባ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል ድርጅቱ አስጠንቅቋል፡፡

ደርጅቱ የአፍሪካ መሪዎች ከምንም በላይ ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ ቅድሚያ እንዲሰጡ ጫና እናሳድራለንም ብሏል፡፡የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአፍሪካ የተመዘገበው ኮሮና ቫይረስ ኬዝ ከ1 ነጥብ 5 በመቶ በታች ሲሆን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥርም 0 ነጥብ 1 በመቶ ያህል ብቻ ነው ብለዋል፡፡

አህጉሪቷ ሌሎች ወረርሽኞችን በመከላከል ዙሪያ ያገኘችው ልምድ የኮሮና ቫይረስንም ለመቋቋም ይረዳታል እንዲሁም እስካሁን ድረስ በሌሎች ሀገራት ከታዩት ተፅእኖችም ልትማር ይገባልም ብለዋል፡፡

ዶክተር ቴድሮስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት የቀነሰባቸው ሀገራትም ቢሆኑ ለሁለተኛ ዙር የኮረኖ ቫይረስ ወረርሽኝ እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል፡፡

የበሽታውን ወረርሽኝ ለማስቆም ፈጣን እርምጃዎችን የወሰዱ አና የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የቻሉ ሀገራት አሁንም ቢሆን ፈጣን እና ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በቫይረሱ ምክንያት የተጎዳውን ኢኮኖሚያቸውን ለመመለስ በሚል የእንቅስቃሴ ገደቦችን እያላሉ ያሉ አውሮፓውያን እና አሜሪካ ለህዝባቸው ደህንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ እና ጥንቃቄዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡በተጨሪም እስካሁን የኮሮና ቫይረስን ለማከም ይረዳል በሚል ጥናት ሲካሄድበት የነበረውን የፀረ ወባ መድሃኒት ላልተወሰነ ጊዜ መታጋዱንም ዶክተር ቴድሮስ አስታውቀዋል፡፡

የፀረ ወባ መድሀኒቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ሞት ሊያፋጥን እንደሚችል የሚሳይ ጥናት መውጣቱን ተከትሎ መድሀኒቱ የኮሮና ቫይረስን ለማከም ይረዳል በሚል የሚደረገውን ምርመራ ላልተወሰነ ጊዜ ማገዱን ሮይተረስ ዘገቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *