የደቡብ ሱዳን ፕሬዛዳንት ሳልቫኪር ኮሮና ይዞታል ተብሎ የሚወራበኝ ሀሰት ነው አሉ።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በየማህበራዊ ድረ ገፁ ኮሮና ይዞት ሊታከም ከሀገር ወጥቷል ተብሎ የሚወራብኝ ሁሉ ሀሰት ነው ሲሉ ክደዋል፡፡

ከፕሬዝዳንትነት የስራ ድርሻዬ ልነሳ እንደሆነ በሚወራው ፕሮፓጋንዳም ህዝቡ እንዳይታለልና ሀሳብ እናዳይገባው ሲሉ ደቡብ ሱዳናውያንን አፅናንተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት የሳልቫኪር ምክትል ሪክ ማቻር እና ሌሎች ኮሮናን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሀይል ዘጠኝ አባላት በኮሮና ተይዘዋል፡፡ በአሁን ሰአት ሁሉም ራሳቸውን ለይተው ነው ያሉት፡፡

ኮሮናን መከላከል ካልቻለን ሀገራችን የከፋ ሁኔታ ውስጥ ነው የምትገባው ሲሉም አስጠንቅቀዋል ኪር፡፡የኛ የጤና ስርአት ይታወቃል፡፡

በሌሎች ሀገር እንዳየነው አይነት የኮቪድ 19 ተጠቂ ሀገራችን የሚኖራት ከሆነ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ መስጠት አንችልም ብለዋል፡፡

ለአመታት የዘለቀው የርስ በእርስ ጦርነት የጤና ስርአቱን ይበልጥ ደካማ አድርጎታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡በሱዳን 600 የኮሮና ተጠቂ እንደተመዘገበ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.