ሲንጋፖር ማስኮችን በነጻ በማሽኖች ማከፋፈል ጀመረች፡፡

ሲንጋፖር ማስኮችን ስታከፋፍል ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን አሁን ደግሞ የሽያጭ ማሽኖችን በመጠቀም ማሰራጨት ጀምራለች፡፡

ሲንጋፖር ለሁሉም የከተማ ነዋሪ በነፃ የአፍና የአፍንጫ ጭንብሎችን እየሰጠች ሲሆን ሰዎች በከተማው ዙሪያ ባሉ 400 ያህል የሽያጭ ማሽኖች ጭንብሎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሲንጋፖር ይህንን የአፍና የአፍንጫ ማስኮችን በነጻ ስታቀርብ ለሶስተኛ ግዜዋ ሲሆን በነዚህ ማሽኞች ሲቀርብ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ሲንጋፖር የኮሮና ቫይረስን መቆጣጠር ብትችልም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን በሁሉም የደቡብ ምስራቅ እስያ አከባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የውጭ ሀገር ሰራተኞች ፍልሰት ተከስቷል፡፡

በሀገሪቱ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ 32 ሺህ 343 ሰዎች መያዛቸው ሲረጋገጥ 23 ሰዎች ህይወታው አልፏል፡፡16 ሺህ 444 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.