በእንግሊዝ በአንድ ሆስፒታል ላይ በተደረገ ምርመራ የሆስፒታሉ 40 በመቶ ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡

በእንግሊዝ በዌስተን ሱፐር ማሬ ከተማ የሚገኘዉ ዌስተን ጀነራል ሆስፒታል፣ የድንገተኛ አደጋዎችና የጽኑ ህሙማን ህክምና በመስጠት ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ሆስፒታሉ ከ260 በላይ በሚሆኑ አልጋዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዉ ወደ ሆስፒታሉ ለገቡ ጽኑ ህሙማን የህክምና ክትትል ሲያደርግ ነበር፡፡

ይሁንና ሆስፒታሉ በሰራተኞቹ ላይ ባደረገዉ ድንገተኛ ምርመራ ካሉት 1 ሽህ 800 ሰራተኞች ዉስጥ ወደ 700 የሚሆኑት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በዚህም ሆስፒታሉ አዳድስ የሚመጡ የቫይረሱን ተጠቂዎችን ለጊዜዉ እንደማያስተናግድ አስታዉቋል፡፡

ሆስፒታሉ እንዳለዉ ምርመራዉ የተደረገዉ ለአጠቃላይ ጥንቃቄ እንጂ ምንም አይነት ምልክት ያሳዬ ሰራተኛ እንዳልነበር አስታዉቋል፡፡

ይህም በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ምልክት ሳያሳዩ ለሌሎች የማስተላለፍ እድላቸዉ ከፍተኛ መሆኑን ማረጋገጫ ነዉ ማለቱን ሜይል ኦንላየን ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.