አዲስ የአንበጣ መንጋዎች በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ቀድሞውኑ በኮቪድ -19 እና በጎርፍ መጥለቅለቅ ተጽዕኖ ውስጥ ለወደቁት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ ዋስትና እጦትን እየጨምሩ መሆናቸውን የሰብአዊ ድርጅት ኦክስፋም በአዲስ ሪፖርት ላይ ገልጻል፡፡
ከቅርብ ወራት ወዲህ የአንበጣ መንጋ በኬንያ ፣ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታር ሰብሎችን እንዳወደመ ይገመታል ፡፡
የጎርፍ መጥለቅለቅ ያስከተለው ከባድ ዝናብ አንበጣ ለመራባት ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥረዋል ይላል ድርጅቱ ፡፡
ከቀዳሚው መንጋ 400 እጥፍ ይበልጣል ተብሎ የሚፈራው የአንበጣ መንጋ እህል በሚደርስበት በሰኔ ወር ላይ ይፈለፈላል የሚል ስጋት ተቀምጧል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ ቁጥጥር ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ችግሮችን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እንቅፋት እየሆነበት እንደመጣ ለቢቢሲ ገልፀዋል ፡፡
ባለፈው ሳምንት የአንበጣ መንጋውን መከላከል እንዲችሉ ለጂቡቲ ፣ ለኢትዮጵያ ፣ ለኬንያ እና ለኡጋንዳ የአለም ባንክ 160 ሚሊዮን ዶላር መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም











