“የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ያለ ደጋፊ ማንሳት እንግዳ ስሜት ይፈጥራል” ሄንደርሰን

ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥን በሰፊ ልዩነት እየመራ ነው። ከ1990 በኋላ የመጀመሪያ የፕሩምየር ሊግ ዋንጫውን ለማንሳት የሚያስፈልጉት ከቀሪዎቹ ዘጠኝ ጨዋታዎች ሁለቱን ማሸነፍ ብቻ ነው። ፕሪምየር ሊጉ በሰኔ አጋማሽ ይጀመራል የሚል ተስፋም ሰንቋል።

ሄንደርሰን “የሊቨርፑልደጋፊዎች ትልቅ ልዩነት ይፈጥራሉ ። ይህንን ሁላችንም እናውቃለን “ብሏል። የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኑ አማካይ ከቢቢሲ ራዲዮ 5 ጋር ባደረገው ቆይታ ” ዋንጫውን አሸንፈህ ደጋፊዎች በሌሉበት መረከብ አንዳች እንግዳ ስሜት ይፈጥራል። “በርግጥ ውድድሩ ገና አልተጠናቀቀም። መስራት የሚጠበቅብን ስራ አለ። የውድድር ዘመኑ እስኪጠናቀቅ ከፍ ባለ ደረጃ መጫወታችንን መቀጠል ይኖርብናል።

“የፕሪምየር ሊጉን ብናሸንፍ ደስተኞች እንደምንሆን ግልጽ ነው። ወደ ፊት ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ሲመለሱ ዳግም ይህንን ቀን በፈንጠዝያ እንደምናከብረው እርግጠኛ ነኝ” ብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.