በሕንድ 18 ሽህ ሄክታር መሬት ሰብል ያወደመዉ የበርሃ አንበጣ ከተማ ገብቶ ሰዎችን ሰላም አሳጥቷል፡፡

በሀገሪቱ ባለፋት 25 ዓመታት ዉስጥ አይታዉ የማታዉቀዉ የበረሃ አንበጣ ተከስቶባታል፡፡

ህንድ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባሻገር በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ የተመታች ሲሆን በዚህም ዜጎቿን ከጥፋት ለመታደግ ሩጫ ላይ ነበረች፡፡

ሀገሪቱ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ሆና ሁለት ኢንች የሚረዝምና አስደንጋጭ ቁጥር ያለዉ የበርሃ አምበጣ ተከስቶባታል፡፡

በምዕራብና መካከለኛዉ የሃገሪቱ ክፍል የተሰራጨዉ የበርሃ አንበጣዉ ሰዎች ኮሮናን ለማምለጥ ቤታቸዉ በተቀመጡበት ወቅት ሰብላቸዉን ሙለጭ አድርጎ አጥፍቶ አሁን ወደ ከተማ መግባቱ ተነግሯል፡፡

ከ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ የህዝብ ብዛት ያላት ህንድ ከዚህ ዉስጥ ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት በዚህ ወቅት ምግብና የመጠጥ ዉሃ በአፋጣኝ የሚፈልጉ ናቸዉ፡፡

በሀገሪቱ የተከሰተዉ የበርሃ አንበጣ ደግሞ 35 ሽህ ሰዎችን መመገብ የሚያስችልን የሰብል ምርት በየቀኑ እያወደመ መሆኑ ተገልጧል፡፡እስካሁንም 18 ሽህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሰብልን ሙሉ በሙሉ ማዉደሙ ተገልጧል፡፡

የአንበጣ መንጋዉ በቀን እስከ 81 ማይል በመጓዝ ከፍተኛ የሰብል ዉድመት እያደረሰ መሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በህንድ በኮሮና ቫይረስ 167 ሽህ የሚሆኑ ሰዎች ሲጠቁ 4 ሽህ 800 የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

በጎርፍና አዉሎ ንፋስ አደጋ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት አልባ መሆናቸዉን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *