በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ የተመዘገበዉ ሞት ስምንት ደረሰ

በተጓደኝ ህመም ምክንያት ህክምና ላይ የነበሩ የ62 ዓመት እድሜ ያላቸዉ ወንድ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ በተደረገ ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኃላ የምርመራዉ ዉጤት ሳይደርስ ህይወታቸዉ አልፏል።
በምርመራዉ ዉጤቱ ቫይረሱ እንዳለባቸዉ ተረጋግጧል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 137 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 968 ደርሷል፡፡

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-

~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ5015 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 137 ኢትዮጲያዉያን ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

~ 86ቱ ወንዶች ሲሆኑ 51ዱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።እድሜያቸዉ ከ4 እስከ 75 ዓመት የሆኑ ናቸዉ።

~ የመኖሪያ ስፍራቸዉ 109 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣8 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣1 ሰዉ ከአፋር ክልል፣2 ሰዎች ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣17 ሰዎች ከአማራ ክልል

~ 20 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡

~ 8 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት አላቸዉ፡፡

~ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ 109 ሰዎች ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 101,581 ደርሷል።

~ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 6 ሰዎች አገግመዋል።(ሁሉም ከአዲስ አበባ)

~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 197 ደርሰዋል።

~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ አራት ታማሚዎች አሉ ፡፡

~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 761 ናቸው።

~ የስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.