ናይጀሪያ ትራምፕ ልኬያሁ ያሉት የመተንፈሻ መሳሪያ አልደረሰኝም ብላለች፡፡

የናይጀሪያ የመረጃ ሚኒስትር እንዳለው ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለናይጀሪያ ቃል ገብተው የነበረውን የመተንፈሻ መሳሪያ ልኬያለሁ ማለታቸውን አስተባብሏል፡፡

እስካሁን አንድም የቬንቲሊተር መሳሪያ አልደረሰንም ሲል የናይጀሪያ መንግስት ተናግሯል፡፡

ባለፈው ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ ለምዕራብ አፍሪካ ሀገራት 1 ሺህ ቬንቲትሌተሮችን ልኪኬያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ነው ናይጀሪያ አልደረሰኝም ያለችው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን ቃል የገቡት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 28 ቀን ከፕሬዚዳንት ሙሐሙዱ ቡሀሪ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ ነው፡፡

በወቅቱ ፕሬዝደንቱ ናይጀሪያ ወረርሽኙን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት ውስጥ ሀገራቸው እገዛ እንደምታደርግ አሳውቀው ነበር፡፡

ባለፈው ሳምንት ሚቺጋን ውስጥ በሚገኘው የፎርድ ሞተር አምራች ኩባንያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ፕሬዝደንት ትራምፕ እንዳሉት አሜሪካ ወደ ናይጀሪያ 1 ሺህ ለመተንፈስ የሚረዱ ቬንትሌተሮችን ልካለች ብለው ነበር፡፡

በናይጀሪያ እስካሁን 8 ሺህ 915 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ ሲረጋገጥ 259 ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ሰበብ ህይወታቸው አልፏል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *