ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 76 ቢሊዮን ብር በብድር እና በእርዳታ ማግኘቷን የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ2012 በጀት ዓመት የ 9 ወራት ከውጭ የተገኙ ብድርና እርዳታ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

ሚኒሰትሩ እንዳሉት በ2ዐ12 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከሁለቱም ምንጮች በብድር ብር 42.31 ቢሊዮን የተገኘ ሲሆን በእርዳታ ብር 32.788 ቢሊዮን ተገኝቷል፡፡

በድምሩ ብር 76 ቢሊዮን ብር ፍሰት ተመዝግቧል ተብሏል፡፡

ድጋፉ እና ብደሩም ዓለም ባንክ ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ፣ የግብርና ልማት ፈንድ ፤ የአውሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ይካተታሉ፡፡

ከአለም አቀፍ መንግስታት በትብብር መልክ እንዲሁ ቻይናን ጨምሮ በርካታ ሀገራት የልማት ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ ድጋፍ ማድረጋቸው ተነስቷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *