የትግራይ ክልል አምስት መገናኛ ብዙሃንን ሐሰተኛ ዘገባዎችን ዘግበዋል በሚል ከሰሰ።

የክልሉ የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሰልጣን በጻፈው ደብዳቤ እንዳመለከተው አራት የፌደራል መንግስት ንብረት የሆኑ እና አንድ የክልል መገናኛ ብዙሃንን ከሷል።

ተከሳሽ መገናኛ ብዙሃኖቹም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ የኣማራ መገናኛ ብዙሃን ናቸው።

እነዚህ መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል ያልተፈጠረ ነገር በሀሰት ዘገባዎችን እየሰሩ በመሆኑ ባለስልጣኑ ጉዳዩን መርምሮ እርምጃ እንዲወስድ ተጠይቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.