የአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር ለኤካ ኮተቤ እና ለጳውሎስ ሆስፒታሎች ከ800 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የገዛቸውን የህክምና ቁሳቁስ እና ታብሌቶችን ድጋፍ አደረገ።

ከ800 በላይ የአውሮፕላን አብራሪዎችን በአባልነት የያዘው የአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር (ኢትዮጵያ) ከተመሠረተበት 1965 ዓም ጀምሮ ስለበረራ ደህንነት እንዲሁም ስለአብራሪዎች ሙያዊ ብቃት አና መብት ላይ እየሰራ ያለ ሙያዊ ማህበር ነው።

ማህበሩ በአሁን ሰዓት በአለም ላይ በፍጥነት አና በአስከፊ ሁኔታ እየተዛመተ የመጣውን የCOVID-19 ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን አገራዊ ዝግጅትና ርብርብ ለማገዝ፣ ከአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር አባላት የተሰበሰበ ከስምንት መቶ ሺ (800,000) ብር በላይ በሆነ የገንዘብ መዋጮ ለኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል አና ለጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች አልባሳትና ታብሌት እርዳታ አደርጓል።

የማህበሩ ሊቀመንበር ካፒቴን በረከት አባተ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በቃናነ እያገዙ ላሉ ሁለቱ ሆስፒታሎች 30 ዊንዶውስ ታብሌቶች ፣3 አንድሮይድ ታብሌቶች ፣400 የጤና ባለሙያ አልባሳት ፣400 የቀዶ ጥገና ቀሚሶች እና 400 ቡትስ ጫማዎችን አስረክበዋል።

ካፒቴን በረከት ለድጋፋ መሣካት፤ በገንዘብ፣ በጉልበት አና በሀሳብ ላገዙ የማህበሩ አባላት አንዲሁም በጴጥሮስ ሆስፒታል እና የካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህ አጋጣሚ ሌሎች ተመሳሳይ የሙያ ማህበራትም እንደዚህ አይነት አገራዊ ግዴታዎችን እንዲወጡ ካፒቴን በረከት ጥሪ እናቀርባለን።

የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ያሬድ አግደው በበኩላቸው ከአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.