የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት የአሜሪካ ፖሊሶች ያልታጠቀውን ጥቁር ሰው መግደላቸውን አወገዙ፡፡

በሚኒሶታ ክፍለ ግዛት ሚኒያፖሊስ ከተማ የአሜሪካ ፖሊሶች ምንም የጦር መሳሪያ ባልታጠቀ ጥቁር ሰው ላይ የፈፀሙትን ግድያ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት አውግዘዋል፡፡

ሙሳ ፋኪ ማሀማት በአሜሪካ ህግ አስከባሪ ሀይሎች እጅ በጆርጅ ፍሎይድ ላይ የተፈፀመው ግድያ በጥብቅ እንደሚያወግዙት ገልፀው ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማቸው ለቤተሰቦቹና ለሚወዳቸው ሰዎች ሁሉ መግለፅ እንደሚፈልጉ ነው ቃል አቀባያቸው የተናገሩት

የህብረቱ ሊቀ መንበር በመግለጫቻቸው እንደተገለፁት የአፍሪካ ህብረት ይህንን ድርጊት አሳፋሪ መሆኑን ገልፀው በአሜሪካ በጥቁር ዜጎች ላይ የሚፈፀመውን የዘር መድሎ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ብለውታል፡፡

የ 46 ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድ ሀሰተኛ የባንክ ፅሑፍ ተጠቅመሀል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ከዋለ በኋላ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ በፖሊስ መገደሉ ይታወቃል ሲል ዘ ጃካርታ ፖስት ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *