ደቡብ ኮሪያ 2ኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳሳሰባት አስታወቀች።

ደቡብ ኮሪያ ከአንድ ወር በፊት ከቻይና በመቀጠል ቫይረሱ የተስፋፋባት ሁለተኛዋ አገር ነበረች።

በአገሯም በሁሉም ቦታ የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣል በቴክኖሎጂ በመታገዝ ቫይረሱን እንደተቆጣጠረች እና ይህ ስኬቷ ለዓለም አገራት ጥሩ ልምድ እንደሚሆን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጾም ነበር።

አገሪቱም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ለማንሳት ያስቀመጠችው ቀነ ገደብ ሊነሳ አንድ ቀን ሲቀረው ግን 2ኛ ዙር የቫይረስ ተጠቂዎችን አግኝቻለሁ ብላለች።

የኮሪያ በሽታ መከላከል ማዕከል እንዳስታወቀው በአገሪቱ 79 የኮሮና ተጠቂዎች መገኘታቸውን አስታውቋል።

በ2ኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ከተገኙ 79 ተጠቂዎች ውስጥ 67 ያህሉ በአገሪቱ መዲና ሲኡል ከተማ የተገኙ ናቸው ተብሏል።

እነዚህ ተጠቂዎች በመገኘታቸው ምክንያትም ትያትር ቤቶችን ጨምሮ ሁሉም መዝናኛ ስፍራዎች ለ2 ሳምንት እንዲዘጉ መወሰኑን AP ዘግቧል።

በሲኡል ከተማ የሚገኙ ሁሉም የግል እና የመንግስት ትምህት ቤቶች ላልታወቀ ጊዜ ተዘግተው እንዲቆዩም ተወስኗል ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.