ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3693 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5846 ደርሷል። ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 52 ናሙናዎች (28 ከጤና ተቋም እና 24 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 4 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ከዚህ ባለፈ አንድ በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበረ ሰው ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር […]