ላ ሊጋው ከኮሮና ቫይረስ በኋላ ዳግም የተከፈተ ሁለተኛው የአውሮፓ ትልቁ ሊግ ሊሆን ነው

ባርሴሎና በሰኔ 13 ሪያል ማዮርካን በሚገጥምበት ጨዋታ ይመለሳል:: የውድድር ዘመኑ በኮሮና ቫይረስ ከመዘጋቱ በፊት ባርሴሎና ያደረገው የመጨረሻ ጨዋታ ሪያል ሶሲዬዳድን ያሸነፈበት ነበር፡፡ በስፔን እግር ኳስ ከመጋቢት 12 ጀምሮ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ከቆመበት እንዲጀምር ይሁንታ ሰጥተዋል፡፡

የውድድር ዘመኑ ዳግም ተመልሶ ከሚደረገው የሪያል ቤቲስ እና ሴቪያ ጨዋታ ሁለት ቀናት በኋላ ባርሴሎና ሪያል ማዮርካን ለመግጠም ይጓዛል፡፡ ከ27 ጨዋታዎች በኋላ ከመሪው ባርሴሎና በሁለት ነጥቦች ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ስፍራ ላይ የተቀመጠው ሪያል ማድሪድ በበኩሉ በሰኔ 14 ኤይባርን ይገጥማል፡፡ የላ ሊጋው አለቃ ሃቪዬር ቴባስ የውድድር ዘመኑ እስኪጠናቀቅ ድረስ በየእለቱ ቢያንስ አንድ ጨዋታ ይኖራል ብለው ነበር፡፡

የላ ሊጋው አዘጋጆች ግን እስካሁን የለቀቁት የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሳምንታት ጨዋታዎች መርሃግብሮች ብቻ ነው፡፡ ባርሳ ቀጣይ ጨዋታውን ደግሞ በሰኔ 16 ከሌሃኔስ ጋር ያከናውናል፡፡ ሪያል ማድሪድ በሰኔ 18 ቫሌንሲያን ይገጥማል፡፡

ላ ሊጋው ከኮሮና ቫይረስ በኋላ ዳግም የተከፈተ ሁለተኛው የአውሮፓ ትልቁ ሊግ ይሆናል፡፡ ቡንደስሊጋው በግንቦት ወደ ውድድር ተመልሷል፡፡ ፕሪምየር ሊጉም በሰኔ 17 እንደሚመለስ ተስፋ ተደርጓል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *