የሬድ ቡል ሳልዝበርጉ አለቃ ኤሲ ሚላንን ለመቀላቀል ከመቼውም ጊዜ በላይ ተቃርበዋል፡፡ የጣሊያን እግር ኳስ የዝውውር ኤክስፐርቱ ጂያንሉካ ዲ ማርዚዮ ከስካይ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ በሁለቱ ወገኖች መካከል በዚህ ሳምንት ስምምነት ሊፈጸም እደሚችል ተናግሯል፡፡
አሁንም ድረስ ግን ራንግኒክ በኤሲ ሚላን የሚይዙት የትኛውን ሚና እንደሆነ አልታወቀም፡፡ የቀድሞው የሆፈንሄይም አሰልጣኝ ወደ ሚላን የሚመጡት የስቴፋኖ ፒዮሊ ተተኪ ለመሆን እንደሆነ ቢነገርም የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው ሊሰሩ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ተነግሯል፡፡
በየትኛውም መንገድ ቢሆን የስፖርት ዳይሬክተሩ ፓውሎ ማልዲኒ ከሃላፊነት መነሳቱ አይቀርም ተብሏል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
በአቤል ጀቤሳ
ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም











