በመጨረሻ ኢግሃሎ በዩናይትድ ኮንትራቱን አራዘመ::

የአጥቂ መስመር ተሰላፊው ኦዲዮን ኢግሃሎ እስከ ጥር 2021 በዩናይትድ የሚያቆየውን የኮንትራት ማራዘሚያ ተፈራረመ፡፡ የ30 ዓመቱ ኢግሃሎ የቻይናውን ሱፐር ሊግ ክለብ ሻንግሃይ ሼኑዋ ለቅቆ እስከ ግንቦት 31 በሚቆይ የውሰት ውል ዩናይትድን የተቀላቀለው ባሳለፍነው ጥር ነበር፡፡

የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ናይጄሪያዊውን አጥቂ በቋሚነት ማስፈረም የሚችልበት አማራጭ ግን አልተካተተም፡፡ ‹‹ የእርሱ ህልም ነበር፡፡ በዚህ ቆይቶ የጀመረውን መጨረስ እና ዋንጫ ማንሳት ይችል ይሆናል ፡፡ ሻንግሃይ ሼኑዋ ድርድሩ በተሳካ መንገድ እንዲጠናቀቅ መልካም ትብብር አድርጓል›› በማለት የዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ስምምነቱ እውን ከሆነ በኋላ ተናግሯል፡፡

ኦዲዮን ኢግሃሎ በዩናይትድ ማሊያ ባደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች አራት ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *