በማጎ ብሔራዊ ፓርክ ስምንት ዝሆኖች በህገወጥ አዳኞች ተገደሉ።

በደቡብ ክልል በሚገኘው በማጎ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በህገ-ወጥ ታጣቂዎች ባሳለፍነው ሳምንት አምስት ዝሆኖች ሲገደሉ ሶስት የሚደርሱ ሌሎች ዝሆኖች ደግሞ መቁሰላችወን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ይሁንና ትናንት በተደረገ አሰሳ ቆስለው የነበሩ ተጨማሪ ሶስት ዝሆኖች እንደሞቱ ማረጋገጣቸውን የፓርኩ ዋርደን አቶ ጋናቡል ቡልሚ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ከተገደሉት ዝሆኖች መካከል ሴት ዝሆኖች እንዳሉበት የነገሩን የፓርኩ ዋርደን እነዚህ ህገወጥ የዱር እንስሳት አዳኞችን ለመያዝ ከበባ ቢያደርጉም በመጨረሻ ማምለጣቸውን እና እስካሁን ድረስም አለመያዛቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በሁሉም ፓርኮች ያሉ ዝሆኖች ከአንድ ሺህ በታች ሲሆኑ በተለይ አሁን ላይ በአንድ ጊዜ 8 ዝሆኖች መገደላቸው የዝሆኖቹን ቁጥር እጅግ እንዲመነምን ያደርገዋለም ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዝሆኖች ጥበቃ ማዕቀፍ ስምምነትን ከፈረሙ አገራት መካከል አንዷ ብትሆንም በየጊዜው የሚፈጸሙ የዝሆኖች ግድያን ማስቆም አልተቻለም።

የማጎ ብሔራዊ ፓርክ ዝሆኖችን ጨምሮ የበርካታ እንስሳት መጠለያ ከመሆኑ በተጨማሪ በእጽዋት ሃብቱም ከፍተኛ ብዝሃህይወት የሚገኝበት ፓርክ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *