በአሜሪካ የተቀሰቀሰዉን ተቃዉሞ በህቡዕ እንዲያረጋጉ እና እርምጃ እንዲወስዱ ከተሰማሩ የጸጥታ አስከባሪዎች መካከል በ60 ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ጥቁር አሜሪካዊዉ ጆርጅ ፍሎይድ በአንድ ነጭ የፖሊስ አባል መገደሉን ተከትሎ በሀገሪቱ የተለያዩ ግዛቶችና ከተሞች ተቃዉሞዎች ተቀስቅሰዋል፡፡

ይህን ተመለከተዉ የትራምፕ አስተዳደርም ተቃዉሞዉን የሚያረጋጉና ካስፈለገም እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ የተሰጣቸዉ የደንብ ልብስ ያለበሱ የጸጥታ አስከባሪ አባላትን በድብቅ አሰማርቶ ነበር፡፡

እነዚህ የጸጥታ አስከባሪ አባላት በተሰጣቸዉ ትዕዛዝ መሰረት በዋሽንግተን ዲሲ ለተቃዉሞ የወጡ ሰዎችን ለማረጋገት ሲሞክሩ ከሰልፈኞቹ በተሰነዘረባቸዉ ጥቃት በትንሹ 60 የሚሆኑ የጸጥታ አስከባሪ አባላት ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ፎክስ ኒዉስ ጽፏል፡፡

ለተቃዉሞ ወደ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞችም ያለ ርህራሄ ጣዉላ፣ጠርሙስና በአቅራቢያቸዉ ያገኙትን ነገር ሁሉ ወደ ጸጥታ አስከባሪዎች ሲወረዉሩ እንደነበር ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

በዚህም 11ዱ በአካባቢ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ተወስደዉ ህክምና የተደረገላቸዉ ሲሆን ለህልፈተ-ህይወት የሚያሰጋ ጉዳት የደረሰበት ሰዉ ግን የለም ነዉ የተባለዉ፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በነጩ ቤተ-መንግስት ዉስጥ ሆነዉ በሚሰሙት የተቃዉሞ ድምጽና በአካባቢዉ የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ በሚያቃጥሉ ሰዎች በእጅጉ መረበሻቸዉን መናገራቸዉንም ዘገባዉ ጨምሮ ገልጧል፡፡

የከተማዋ ከንቲባ ሙሬል ቦዉሴር የተሰማሩት የጸጥታ አስከባሪ አባላት ለጋራ ደህንነት በመሆኑ ሰልፈኞቹ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *