በጆርጅ ፍሎይድ ሞት ሳቢያ በአሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍ በመላ አገሪቱ የተሰራጨ ሲሆን አለመረጋጋት ቀጥሏል፡፡

ከ24 በላይ የአሜሪካ ከተሞች በተቃውሞ እየተናጡ ሲሆን 12 ግዛቶችን ጨምሮ ከዋሽንግተን ዲሲ ውጪ ባሉት ከተሞች በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ጥቃት እየተሰነዘረ ነው፡፡

ለጥቁር አሜሪካዊው ግድያ ፍትህ የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች በአሜሪካ ከልክ ያለፈ ሀይል እየተጠቀሙ መሆኑም ተዘግቧል፡፡

በአሜሪካ ከ24 በላይ ከተሞች በእቅስቃሴ ገደብ ላይ ናቸው፡፡ የሀገሪቱ የብሐየራዊ ጥበቃ ወታደሮችም ተሰማርተዋል፡፡

ሲ ኤን ኤን ፕሬዘዳንቱ በጉዳዩ ዙሪያ ሀገሪቱን ለማረጋጋት ያለቸው እቅድ ምንድን ነው ብሎ ጠይቆ ነበር፡፡ የደህንነት አማካሪው ሮበርት ብሬን ፕሬዘዳንቱ በጉዳዩ ዙሪየቃ ቀደም ሲል ተናግረዋል በማለት መልሰዋል፡፡

ትራፕ የፍሎይድን ሞት አውግዘዋል፡፡ በንግግራቸውም እኛ መልስ እንዲሰጣቸው ከሚጠይቁት ሰልፈኞች ጋር ነን ፤ የህዝቡንም አመፅ ማስቆም አለብን ማለታቸውን ብሬን አንስተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.