ቼልሲ የአያክሱን የግራ መስመር ተከላካይ ኒኮላስ ታግሊያፊኮ የማስፈረም ጥረቱን ገፍቶበታል::

ቼልሲ ታግሊያፊኮ ላይ ዓይኑን ጥሏል ቼልሲ የአያክሱን የግራ መስመር ተከላካይ ኒኮላስ ታግሊያፊኮ የማስፈረም ጥረቱን ገፍቶበታል፡፡ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ይዞት ወጣው ዜና ቼልሲ የግራ መስመር ተከላካዩን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቧል ብሏል፡፡

ሰማያዊዎቹ በመጪው ክረምት አዲስ የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ቆርጠዋል፡፡ ቤን ቺልዌል እና አሌክስ ቴሌስም ከቼልሲ ጋር ተያይዞ ስማቸው የተጠቀሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ ቼልሲ ተጫዋቹን ለመውሰድ ከባርሴሎና እና አርሰናል ብርቱ ፉክክር ማድረግ ይጠበቅበታልም ተብሏል፡፡

ታግሊያፊኮ በዚህ የውድድር ዘመን አምስት ጎሎችን አስቆጥሮ ሰባት ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *