የደቡብ ክልል ሶስተኛውን የኮሮና ቫረስ መመርመሪያ ማዕከል በአርባምንጭ ከፈተ፡፡

በክልሉ እስካሁን ሁለት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ላብራቶሪዎች ሲኖሩ በዛሬው እለት ሶስተኛው የሳውላ ምርመራ ማዕከል ስራውን እንደሚጀመር የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ አጥናው ካውዛ ለኤትዩ ኤፍ ኤም አሳውቀዋል፡፡

እኚህ ምርመራ ማዕከላት እያንዳንዳቸው እስከ 200 ናሙናዎችን የመመርመር አቅም አላቸው፡፡

ወረሽኙ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ቀድሞ ለመቀነስ የመመርመር አቅምን ማሳደግ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው የሚሉት አቶ አቅናው በአርባ ምንጭ ሳውላ ዛሬ ስራውን የሚጀምረው የምርመራ ማዕከል አቅማችንን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በሀዋሳ ፤ወላይታ ሶዶ አሁን ደግሞ በሳውላ የተጀመረው ምርመራ ማዕከል በቀን 500 ናሙናዎችን መርመር ያስችለናል ይላሉ አቶ አቅናው፡፡

በቀጣይም በሀዲያ ሆሳዕና ፤በሚዛን አማን እና ሌሉች የክልሉ አከባቢዎች ላይ የምርመራ ማዕከላትን በፍትነት ስራ እንዲጀምሩ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ክልል እስካሁን 13 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ስድስቱ አገግመው ተመልሰዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ግንብት 24 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.