ሀገሪቱ ከሰል ለምግብ ማብሰያ አገልግሎት እንዳይውል በዋና ከተማዋ ኪጋሊ ላይ ያገደች ሲሆን ከሰል ከሀገሪቱ ገጠራማ ክፍል ወደ ከተማዋ እንዳይገባ የሚስችል ገደቦችንም አስቀምጣለች፡፡
ይህ የከሰል አትጠቀሙ ገደብ የሀገሪቱን የደን ሀብት በህገወጥ የከሰል ንግድ ከተሰማሩ ሰዎች ለመጠበቅ የታለመ ነው ተብሏል፡፡ በአማራጭነት ሰዎች ከከሰል ይልቅ ጋዝን እንዲጠቀሙ እያበረታታች ትገኛለችም ተብሏል፡፡
ሩዋንዳ ከኬኒያ እና ኡጋንዳ በመቀጠል ከሰል አገልግሎት ላይ እንዲውል ከምታበረታታ ሀገራት መካከል ትጠቀሳለች፡፡
ይህም በከሰል ጭስ አማኝነት በየዓመቱ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ለመተንፈሻ አካላት ህመም እንዲዳረጉ ከሚያደርጉት ሀገራት ጎራ መድቧታል፤ ስትወቀስበትም ኖራለች፡፡
ህገወጥ የከሰል ንግዱ በሰዎች ላይ ከሚያደርሰው የጤና ጉዳት ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥም እያስከተለ ነው በሚል ሀገሪቱ ትወቃሳለች፡፡
የ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ የሆነችው ዋና ከተማዋ ኪጋሊ ውስጥ 85 በመቶ ያህል ሰዎች ምግባቸውን የሚበስሉት በእንጨት ነው፡፡
ይህንንም ለማስቀረት ሀገሪቱ የታጣለችውን የከሰል አትጠቀሙ እገዳ ተከትሎ ዜጎች የጋዝ አቅርቦቱን በዝቅተኛ ዋጋ እንዲያገኙ አደረጋለሁ ማለቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በትግስት ዘላለም
ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም











